981
Ethiopia: የዕለቱ ዜናዎች Daily Ethiopian News -Addis Post 08/31/20
- የ ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚፈፀም የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ ጋር በተያያዘ ያደረገውን ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል።
የጥናቱ ውጤት ዋነኛ ይዘት ከዚህ በታች ተቀምጧል።
በአዲስ አበበ ከተማ መሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ ጥናት አንኳር
• የከተማው አስተዳደር እያየና እየሰማ በሕገ ወጥ እና በተደራጀ መልኩ በወረራ የተያዙ ቦታዎች በፍጥነት ካርታና ፕላን ተሰርቶላቸው ለ3ተኛ ወገን በሽያጭ ተላልፈዋል። በማኅበር እና በግል ለማምረቻና ለንግድ አገልግሎት እንዲውሉ ተደርገዋል፤ በምንም መስፈርት የቤት ተጠቃሚ ሊሆኑ የማይገባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ቤት እና የነዋሪነት መታወቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
• በዋናነት በመሬት ወረራው ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበሩት ሰዎች የአርሶ አደር ልጆች ነን የሚሉ፤ ቦታዎቹ ከዚህ ቀደም የቤተሰቦቻችን መሬቶች ናቸው፤ በቂ ካሳ ሳይከፈለን ከቦታችን ተነስተናል የሚሉ ግለሰቦች እና ወረራ የተፈፀመባቸው ቦታዎች አካባቢ ላይ የሚገኙ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ኃላፊዎች ናቸው፡፡
• ይህ በጠራራ ፀሐይ በተደራጀ መልኩ የተፈፀመው የመሬት ወረራ በመንግሥት ሥልጣን ላይ ያሉ አመራሮች፤ የፍትህና ፀጥታ አካላት ተጠሪዎች ከፍተኛ እገዛ የተደረገበት ብቻ ሳይሆን እነዚህ አካላት የጉዳዩ ዋና ተዋንያን ነበሩ። በተለያየ መልኩ ሊጠቅሟቸው ለሚፈልጉ ግለሰቦች፣ ቡድኖች እና አደረጃጀቶች መሬቱን ወረው እንዲይዙ አመቻችተዋል፤ የመንግሥትን ሥልጣን ለሕገ ወጥ ተግባር ከለላ እና ሽፋን እንዲሆን አድርገዋል፤ ከዚህም ባስ ሲል ከግለሰቦች ጋር በመመሳጠር እራሳቸው ወረራ ፈፅመዋል።
• በጠቅላላው 213,900 ካ.ሜ ያህል ስፋት ያለው ቦታ ጥናቱ ባያቸው ጥቂት ቦታዎች ላይ ብቻ መወረራቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።
• ከጋራ መኖሪያ ቤት ጋር በተገናኘም በግልፅ የታየው የመንግሥት አካላት ሕገ ወጥ ተግባር ነው። ኢፍትሐዊ ሕጎችን እና መመሪያዎችን በማውጣት እና ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ሕጎችን እና ደንቦችን በማሻሻል ለካቢኔው እና ለከንቲባው በተሰጠ ልዩ ሥልጣን ከንቲባውም ሆነ ካቢኔያቸው ቤቶችን እንደፈለጉ እንዲያድሉ ምክንያት ሆኗል።
• በዚህ መሠረት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቢሮዎች ሳር ቤት አካባቢ ከሚገኘው ጽሕፈት ቤት ሁሉም የተመዘገቡ ሠራተኞች በሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ብዙ ሺህ ቤቶች የድልደላ እጣ የወጣላቸው ሲሆን፣ የድልድል እጣ ለደረሳቸው ሰዎች ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ድልድል ተደርጎላቸዋል፡፡ በዚህ ቀን ሁሉም ሠራተኞች የኮንዶሚኒየም ብሎክ ቁጥር እና የቤቱን ቁጥር በስማቸው ተረጋግጦ የተሰጣቸው ሲሆን፣ በተሰጣቸው የቤት ቁጥር የነዋሪነት መታወቂያ የተዘጋጀላቸው መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡
• የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንጻዎች ውስጥ የተሠሩ የንግድ ቤቶች በተመለከተ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች፣ ልጅ እና የልጅ ልጅ ተብለው በገፍ ስለመታደላቸው፤ በእግር ኳስ ደጋፊነት ስም ለተሰባሰቡ ማኅበራት መከፋፈላቸው ተጨባጭ ማስረጃዎች ተገኝተዋል፡፡
Ethiopia: የዕለቱ ዜናዎች Daily Ethiopian News -Addis Post 08/31/20 Watch daily updated Ethiopian news from a reliable and balanced source. Addis Post is an independent Ethiopian related News and other programs, producer.
Visit us https://addisMedia.net Subscribe to our channel to follow everything related to Ethiopia. AddisPost Daily Ethiopian News Source #Ethiopia #EthiopianNews