870
ሐሰት፡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በፌስቡክ በኩል የማስጠቀቂያ መልእክት አላስተላለፉም
በ ጥቅምት 2 ፣ 2014 (October 12, 2021) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ ስም የተከፈተ የፌስቡክ ገጽ “…..በየቡና ቤቱ የሰራዊቱንም ሆነ የአመራሩን ስም ከማጉደፍ እንጠንቀቅ።” የሚል መልእክት ርዕሰ መስተዳድር እንዳስተላለፉ አድርጎ አሰራጭቷል።
አዲስ ሚዲያ ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር ባካሄደው የማህበራዊ ሚዲያ ቅኝት የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ስያሜ በመጠቀም ከ 20 በላይ የፌስቡክ ገጾች መከፈታቸውን አረጋግጧል።
ሆኖም ከተከፈተ ጥቂት ቀናት የሆነውና ከ 7 ሺ 800 በላይ ተከታዮች ያገኘው ከላይ የተገለጸው የፌስቡክ ገጽ ዶ/ር ይልቃል “የሰራዊቱንም ሆነ የአመራሩን ስም ከማጉደፍ እንጠንቀቅ።” በሚል መልእክት እንዳስተላለፉ አድርጎ ያቀረበው መረጃ ሐሰት እንደሆነ ተረጋግጧል።
የአማራ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ ምንም አይነት የፌስቡክ ገጽ እንደሌላቸው ገልጿል።
በመሆኑም የክልሉን ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዋቢ በማድረግ የፌስቡክ ገጹ ሐሰተኛ እንዲሁም መረጃው በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የተጻፈ አለመሆኑ ታውቋል።
ይህ የእውነታ ማጣራት በአዲስ ሚዲያና ኮድ ፎር አፍሪካ ትብብር የቀረበ