1.3K
ሐሰት፡ የትግራይ ቲቪ እና ህወሓት ያወጧቸው ምስሎች ሐሰተኛ ናቸው
ህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በኩል ዛሬ (ህዳር 2፣2014 አ/ም) “ጀግናው የትግራይ ሰራዊት በሚሌ ግንባር የጦር ሄሊኮፕተርን መጣሉን አስታወቀ” በሚል ከታች የሚታየውን ምስል አጋርቷል።
በተመሳሳይ የትግራይ ቴሌቭዥን በይፋዊ ፌስቡክ ገጹ በኩል ይሄንኑ መረጃ በትግርኛ ቋንቋ ከሌላ ምስል ጋር ለጥፏል።
አዲስ ሚዲያ በሃቅ ማንጠሪያ ክፍሉ በኩል ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር ከዘገባዎቹ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ሁለት ምስሎች ላይ የማጣራት ስራ ያከናወነ ሲሆን በዚህም ሐሰተኛ መሆናቸውን አረጋግጧል።
ትግራይ ቴሌቭዥን ከሰአታት በኋላ ምስሉ ከጉግል እንደተወሰደ በመግለጽ ማስተካከያ አድርጓል።
በማጣራት ሂደቱ አዲስ ሚዲያ የጉግል ምስል ማሰሻን (Google reverse image search) የተጠቀመ ሲሆን ፥ ህወሓት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ “…የትግራይ ሰራዊት በሚሌ የጦር ሄሊኮፕተር መጣሉን አስታወቀ” ከሚል መረጃ ጋር ያጋራው ምስል በጎርጎሮሲያኑ የዘመን አቆጣጠር በ 2016 በኢራቅ የነበረውን ሁኔታ በተመለከተ የእንግሊዙ ዘታይም ድረ-ገጽ የተጠቀመው መሆኑን አመላክቷል።
በሌላ በኩል የትግራይ ቴሌቭዥን የተጠቀመው ምስል ጷግሜ 3፣2008 (September 8, 2016) ታስ በተባለ የፎቶ ባለሙያ የተነሳ መሆኑን ግዙፉ የምስል ማከማቻ ‘Alamy’ ከታች እንደሚታየው አረጋግጧል።
በመሆኑም ከላይ የተገለጹትን ማስረጃዎች ዋቢ በማድረግ ህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) እና ትግራይ ቴሌቭዥን በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው የተጠቀሟቸው ምስሎች ሐሰተኛ መሆናቸውን አረጋግጠናል።
ይህ የእውነታ ማጣራት በአዲስ ሚዲያና ኮድ ፎር አፍሪካ ትብብር የቀረበ